Топ-100
Back

ⓘ ፍልስፍና - የሳይንስ ፍልስፍና, ኅልውነት, ማኅበረሰባዊ ፍልስፍና, ፔሪፓቶስ, የፕላቶ አካዳሚ, ሌብኒትዝ, ምክኑያዊነት, ህሊና, ሒስ, ቁሳዊነት, ንቃተ ህሊና, ካይዘን ..                                               

የሳይንስ ፍልስፍና

የሳይንስ ፡ ፍልስፍና የሳይንስ መሠረቶችን ፣ ዘዴዎችን እና መዘዞችን በጥልቀት የሚያጠና የፍልስፍና ዘርፍ ነው። ሳይንስን ከሌሎች የ ዕውቀት ዓይነቶች የሚለየው ምንድን ነው? ምን ዓይነት ዕውቀት ሳይንስ ሊባል ይችላል? ምን ዓይነትስ አይባልም? የሳይንስ ጽንሰ ሓሳቦች የቱን ያክል አስተማማኝ ናቸው? የዚህ ሁሉ የሳይንስ ዕውቀት የመስተጨረሻ ግብ ምንድን ነው? የሰውን ህይወት ማሻሻል ነው? ወይንስ ስለከባቢ ዓለም ዕውነትን ለማዎቅ ነው? እነዚህ ጥያቄዎች የዚህ ፍልስፍና ዋና ትኩረት ናቸው። ተጨባጩን ዓለም ለመገንዘብ በተደረጉ ጥረቶች፣ ከጥንት ጀምሮ ብዙ ዓይነት ሐሳቦች ፈልቀዋል። እነዚህ ጥረቶች፣ በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት ምናባዊን አለም፣ መናፍስትንና እና ሌሎች ተጨባጭ ያልሆኑ ነገሮችን ያሳተፉ ነበሩ። ሆኖም ቀስ በቀስ፣ አንዳንድ ፈላስፋዎች እነዚህ ለሽህ ዓመታት የተሰራባቸው ሐሳቦች ከባድ ስህተት እንዳለባቸው ፤ ይባስ ብሎም ለቀጣይ የመሻሻል እርምጃ እንቅፋት እንደሆኑ ማሳዎቅ ጀመሩ። ይህ የተጠራቀመ ትችትና ቅሬታ በአውሮጳ የሳይን ...

                                               

ኅልውነት

አብዛኞች ሃይማኖቶችና ፍልስፍናወች የሰው ልጅ ኅይወት ትርጉም አለው ብለው ያምናሉ። ስለሆነም ይህን አላማ ወይም ለማስፈጸም ወይም ደግሞ ለማግኘት ሲጥሩ ይታያሉ። ከዚህ በተጻራሪ በ ኅልውነት ፍልስፍና የሰው ልጅ ህይወት ከመፈጠሩ በፊት የተጻፈ ትርጉምም ሆነ አላማ የለውም። ስለሆነም የፍልስፍና አትኩሮት መሆን ያለበት "እያንዳንዱ ግለሰብ ለህይወቱ እንዴት ትርጉምና አላማ መስጠት አለበት?" የሚል ነው። የኅልውነት ፍልስፍና አባት ነው የሚባለው ሶረን ኬርከጋርድ እንዳስቀመጠው "እያንዳንዱ ግለሰብ ለህይወቱ ትርጉም የመስጠት እንዲሁም ይህን ህይወቱን በሃቀኝነትና በሙሉ ስሜት የመምራት ኃላፊነት አለበት።" ይህ ሲሆን ታዲያ ተስፋ መቁረጥ፣ የኅልውና ድንጋጤ፣ ባይተዋርነት፣ ድብርትና መሰረተ ቢስነት የተባሉ የኅልውና ቀውሶች የሰውን ልጅ ይጋረጣሉ፣ እኒህን እንቅፋቶችን የማሸነፍ ዘዴ መቀየስ የኅልውነት ፍልስፍና አይነተኛ አትኩሮት ነው። የሰው ልጅ ህይወት ትርጉም የለሽና አላማውም የማይታወቅ ሲሆን ትርጉም አለው እምንለው እያንዳንዱ ግለሰብ ለህይወ ...

                                               

ማኅበረሰባዊ ፍልስፍና

ማኅበረሰባዊ ፍልስፍና በሰው ልጅን ማኅበራዊ ባህርይ ላይ የሚመራመር የፍልስፍና ዘርፍ ነው። የማሕበራዊ ማንነት፣ የፖለቲካዊ ሥነ ምግባር፣ የተለያዩ ር ዕዮተ ዓለሞችን፣ የሚዎጡ ኅግጋት ፍትሃዊነትን፣ የሥነ ልቡናን ፍልስፍናዊ መሰረቶች፣ እና መሰል የቡድን ጠባያትን የሚያጠና ክፍል ነው። በዚህ የ ዕውቀት ሥር ከሚካለሉ ውስጥ፣ ማኅበራዊ ሥነ ኑባሬ እና ማኅበራዊ ሥነ ዕውቀት እንደ ቅርንጫፍ ሊዎሰዱ ይችላሉ። በማኅበራዊ ሥነ ኑባሬ "ማኅረሰቦች ኑባሬ አላቸውን? አንድ ማኅበረሰብ አለ ከተባለ፣ በውስጡ ካሉት አባላት ግለሰቦች ይለያል? ከተለየስ በምን ዓይነት ሁኔታ?" የሚሉት ጥያቄዎች ይመረመራሉ። በማኅበራዊ ሥነ ዕውቀት "የአንድ ግለሰብ ዕውቀት በማኅበረሰቡ የቱን ያክል ጫና ይደረግበታል? ማኅበራዊ ተቋማት በአንድ ግለሰብና በአጠቃላይ ማኅብረሰቡ ዕውቀትና እምነት ላይ ምን አስተዋጽዖ ያደርልጋሉ?" የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ይሞክራል። ስለሆነም ይህ የፍልስፍና ዘርፍ ከፖለቲካ እና ሥነ ባሕል ጥናቶች ጋር ተነባባሪ ክፍሎች አሉት።

                                               

ፔሪፓቶስ

ፔሪፓቶስ በአቴና፣ ግሪክ አገር በአሪስጣጣሊስ የተመሠረተ ጥንታዊ የከፍተኛ ትምህርት ቤት ተቋም ነበር። ከ343 እስከ 94 ዓክልበ. ድረስ ቆየ። መገናኛ ቦታው በአረመኔ ጣኦት በአፖሎ ቤተ መቅደስ ሊሲየም ነበረ። አሪስጣጣሊስ ከ375 እስከ 355 ዓክልበ. በፕላቶ አካዳሚ አባል ነበረ፣ ከዚያ የራሱን ትምህርት ቤት በሊሲየም ጀመረ። እንደ ዘመናዊ ትምህርት ቤት አስተማሪና ተማሮች ተለይተው ሳይሆን፣ እንደ አካዳሚ ግን ከፍተኛ እና ታቸኛ አባላት ነበሩ። ትምህርቱ በጥያቄና መልስ ይካሄድ ነበር። በተቋሙ ውስጥ ከተማሩት ጥናቶች መካከል በተለይ ፍልስፍና፣ የተፈጥሮ ሕግጋት ጥናትና ሌላ የታወቀ ሳይንስ ዕውቀት ነበሩ። አሪስጣጣሊስ በ330 አክልበ. አረፈና እስከ 296 ዓክልበ. ድረስ የነበሩት አስተዳዳሪዎች ከአሪስጣጣሊስ ፍልስፍና በላይ ምንም ይፋዊ ርዕዮተ አለም አላስተማሩም። ይህም ማናቸውንም ፍልስፍና ወይም ዕውቀት ለመሰብሰብ ነበረ። በ296-277 ዓክልበ. የተቋሙ ሦስተኛ መሪ የሆነው ስትራቶ ዘላምፕሳኮስ ያስተማረው ርዕዮተ አለም የአምላክ ሚና ...

                                               

የፕላቶ አካዳሚ

የፕላቶ አካዳሚ በአቴና፣ ግሪክ አገር በፕላቶ የተመሠረተ ጥንታዊ የከፍተኛ ትምህርት ቤት ተቋም ነበር። ከ395 እስከ 94 ዓክልበ. እና እንደገና ከ402-521 ዓም ቆየ። ቦታው በአቴና ከተማ በቅዱስ የወይራ ደን አጠገብ ነበረ። ግሪካዊ ፈላስፎች በፕላቶ መኖሪያ ይሰብስቡ ጀመር። እንደ ዘመናዊ ትምህርት ቤት አስተማሪና ተማሮች ተለይተው ሳይሆን፣ ከፍተኛ እና ታቸኛ አባላት ነበሩ። ሴቶች አባላትም ነበሩ። ትምህርቱ በጥያቄና መልስ ይካሄድ ነበር። በተቋሙ ውስጥ ከተማሩት ጥናቶች መካከል በተለይ ፍልስፍና፣ ሥነ ቁጥር፣ ሥነ ፈለክ ነበሩ። በመግቢያ ላይ "ከጂዎሜትሪ ተመራማሪዎች በቀር ማንም አይግባ" የሚል መፈክር እንደ ተለጠፈ ተብሏል። አሪስጣጣሊስ ከ375 እስከ 355 ዓክልበ. በዚያ አባል ነበረ፣ ከዚያ የራሱን ትምህርት ቤት ፔሪፓቶስን በሊሲየም ጀመረ። ፕላቶ በ355 አክልበ. አረፈና እስከ 274 ዓክልበ. ድረስ የነበሩት አስተዳዳሪዎች ከፕላቶ ፍልስፍና በላይ ምንም ይፋዊ ርዕዮተ አለም አላስተማሩም። በ274 ዓክልበ. አርቄሲላዎስ ዋና አስተ ...

                                               

ሌብኒትዝ

ጎትፍሪድ ቪልሄልም ሌብኒትዝ 1646 – November 14 1716 እ.ኤ.አ) የ17ኛው ክፍለ ዘመን የጀርመን የሒሳብ ሊቅ፣ ሳይንቲስት፣ ፈላስፋ፣ ፍርድ አጥኝና ባጠቃላይ መልኩ ሁለ ገብ ተመራማሪ ነበር። ሌብኒዝ ከኢሳቅ ኒውተን ትይዩ ካልኩለስ የተባለውን የዕውቀት ዘርፍ ፈጥሯል። አሁን ድረስ ተማሪወች የሚጠቀሙበት የካልኩለስ የአጻጻፍ ስልት በዚህ ሰው የተፈለሰፈ ነው። ለኮምፒዩተር ስራ እጅግ ወሳኝ የሆነውን የሁለትዮሽ ቁጥር ስርዓት ዘመናዊ ኮምፒዩተሮች ከመሰራታቸው 300 አመት በፊት ፈልስፏል። በፍልስፍናው ዘርፍም ጠለቅ ያለ አስተዋጽኦ አበርክቷል። የሌብኒዝ ፍልስፍና እንደ ደካርት ፍልስፍና ቀልበኛ ይባላል። "ይህ ዓለም እግዚአብሔር ሊፈጥራቸው ይችላቸው ከነበሩ ዓለማት ሁሉ የተሻለ" ነው የሚለው ድምዳሜው የሌብኒዝን ፍልስፍና ብሩህ ተስፈኛ በሚባል መደብ ስር እንዲታወቅ አድርጎታል። የሌብኒዝ ፍልስፍና የቀደምት አውሮጳውያን የፍልስፍና ዘዴ ተብሎ የሚታወቀውን ስኮላስቲክ ወደ ኋላ የሚመለከትና ወደፊት ደግሞ በ20ኛው ክ/ዘመን ብቅ ያሉን ዘ ...

                                               

ምክኑያዊነት

ምክኑያዊነት ዕውቀት የሚገኘው በመሪ ሐሳቦች እና በምክንያት ነው የሚል የሐሳባዊ ዓይነት ፍልስፍና ነው። በጥሩ አመክንዮ ሊደረስባቸው የማይችሉ ዕውቀቶችን፣ ለምሳሌ ሥሜታዊነትን፣ ሃይማኖታዊ ተዓምራትን፣ ከሕዋሳት የሚፈልቁ ግንዛቤዎችን፣ ባጠቃላይ መልኩ አይቀበልም። አንድ አውሮፕላን፣ መሬት ላይ እያለ ግዙፍ ቢመስልም፣ አየር ላይ ሲዎጣ ጥንጥ ይመስላል። ነገር ግን ማንም እንደሚገነዘብ የአውሮፕላኑ ግዝፈት ምንጊዜም እኩል ነው። ይህን የአለመቀያየር ሁኔታ እምናውቀው በሚዋሸን የሥሜት ሕዋሳታችን ዓይናችን ሳይሆን በአዕምሮ ውስጥ ባለን የተፈጥሮ የአስተሳሰብ መርህ ነው ያላል ምክኑያዊነት። ከዚህ የፍልስፍና ዓይነት ትይይዩ የሚቆመው ፍልስፍና፣ ዳሳሻዊነት ሲባል፣ ስለ ዓለም እምናውቀው ዓለምን በሕዋሶቻችን በመመርመር እንጅ ውስጣዊ መሪሃሳቦችን በምክንየት በማያያዝ አይደለም ያላል።

                                               

1994

1994 አመተ ምኅረት ጳጉሜ 5 ቀን - ገለልተኛ አገር የሆነ ስዊስ በመጨረሻ የተባበሩት መንግስታት አባል ሆነ። መስከረም 1 ቀን - አራት አውሮፕላኖች በአረብ ተዋጊዎች ተሰርቀው በአለም ንግድ ሕንጻና በፔንታጎን ተጋጭተው 3000 ያህል ሰዎች ተገደሉ። ነሐሴ 20 ቀን - የምድር ጉባኤ ስብሰባ በጆሃነስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ጀመረ። ሐምሌ 2 ቀን - የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ተፈትቶ በአፍሪካ ኅብረት ተተካ። ነሐሴ 4 ቀን - የሳምንት ቀኖችና የወር ስሞች ሁሉ በቱርክመንኛ እንደ ቱርክመኒስታን መሪ አቶ ሳፓርሙራት ኒያዞቭ "ሩህናማ" የሚባል ይፋዊ መጽሐፍ ፍልስፍና በአዋጅ ተቀየሩ።

ህሊና
                                               

ህሊና

ህሊና ጥሩና መጥፎን መለየት የሚችል የአዕምሮ ክፍል ነው። አንድ ሰው ለአንድ ድርጊት ከሚሰጠው ዋጋ አንጻር ይመጣል። ይህ ማለት አንድ ግለሰብ ያለውንና ያመነበትን የሥነ ምግባር ዋጋ ጥሶ በተቃራኒ ሲሄድ የራሱ አዕምሮ እንዲወቅሰው የሚያደርገው የዚያ ሰው ህሊና ነው ይባላል። ደግሞ ይዩ፦ የኅሊና ነፃነት

ሒስ
                                               

ሒስ

ሒስ ማለት የአንዱን ነገር ወይም አካሄድ ዋጋ ወይም ጉድለት መተቸት ወይም ማመልከት ነው። ሓያሲ በእንግሊዝኛው አጠራር "ክሪቲክ" critic በመባል የሚታወቀው ሐሳብ ገባሪውንም ያመለክታል። በአማርኛ ሒስ የግብሩ፣ ሐያሲ ደግሞ የገባሪው መጠሪያ ሆኖ ያገለግላል ። ግብሩ ግምገማ፣ ግምት፣ ፍርድ፤ ገባሪው ደግሞ ገምጋሚ፣ ገማች፣ ፈራጅ ማለት ነው።

                                               

ቁሳዊነት

ቁሳዊነት ዓለም በሙሉ አካላዊ ናት፣ ከዚህ ውጭ ምንም ነገር በዓለም የለም የሚል የፍልስፍና ዓይነት ነው። ይህ አስተሳሰብ ከቁስ አካላዊነት ጋር በጣም የተቀራረበ ሲሆን ትንሽ የሚለየው አቅምን እና የተፈጥሮ ኅግጋትንም ከቁስ አካላት ጋር አብሮ ስለሚቀበል ነው።

ንቃተ ህሊና
                                               

ንቃተ ህሊና

ንቃተ ህሊና ማለት "የሚገነዘብ"፣ "ስሜትን የሚረዳ" ፣ "እኔነትን በውል የሚለይ"፣ ወይም ደግሞ ሙሉ አዕምሮን የሚቆጣጠር የሚሉ ብዙ ትርጓሜወች አሉት። ስለሆነም ንቃተ ህሊና ብዙ የአዕምሮ ተግባራትን በጃንጥላው ስር የሚያስተናግድ ክፍል ነው።

ካይዘን
                                               

ካይዘን

ካይዘን የአመራር ፍልስፍና ነው። ከጦርነቱ በኋላ በጃፓን ድርጅቶች ተለማ። በአንዳንድ ኢንዱስትሪ በተለይም በአንዳንድ መኪና ፋብሪኮች በተግባር ውሏል። የካይዘን ፍልስፍና ዘዴ በአጭሩ "ማቀድ -> ማድረግ -> ማመልከት -> መገሰብ/ማስተካከል" ይባላል። በተጨማሪ ማናቸውም ዕንቅፋት በደረሰ ጊዜ የሥሩን ጠንቅ ለማወቅ አምስት ጊዜ "ለምን" መጠይቅን ያስተምራል። እያንዳንዱ ምክንያት ላይኛ ምክንያት እንዳለው በማሠብ። እንዲህ ሲደረግ አንድ የሚታወስ መርኅ "የሚጎደለው ሂደቱ እንጂ ሰዎቹ አይደሉም" ነው ይባላል። የ "ካይዘን" ትርጉም ከጃፓንኛ እንዲያውም "ማሻሻል" ሲሆን፣ ብዙ ጊዜ ፅንሰ ሀሣቡ እንደ "ምንጊዜም ማሻሻል" ይተረጎማል።

Free and no ads
no need to download or install

Pino - logical board game which is based on tactics and strategy. In general this is a remix of chess, checkers and corners. The game develops imagination, concentration, teaches how to solve tasks, plan their own actions and of course to think logically. It does not matter how much pieces you have, the main thing is how they are placement!

online intellectual game →