Топ-100
Back

ⓘ ኢትዮጵያ - ኢትዮጵያ, መንግሥተ ኢትዮጵያ, አርጎብኛ, አቡጊዳ, ኢትዮጵስት በዓለም ዙሪያ, ኩሽ, የካም ልጅ, ቅደሚ, ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን, ጳጉሜ, ጥር, ነሐሴ, አበሻ ስም, ኢንተርኔት በኢትዮጵያ, የኢትዮጵያ መጓጓዣ, የኢትዮጵያ ብሄራዊ አርማ ..                                               

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ወይም በይፋ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በአፍሪካ ነፃነታቸውን ጠብቀው ለመኖር ከቻሉ ሁለት አገሮች አንዷ ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን ፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ናት። አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ዕድሜያቸው ከአንድ ምዕተ-ዓመት የሚያንስ ሲሆን ፣ ኢትዮጵያ ግን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በንጉሠ-ነገሥታት እና ንግሥተ-ነግሥታት የተመራች ሀገር ናት። የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት የአመጣጡን ዘር እስከ አስረኛው ዓመተ-ዓለም ድረስ ይቆጥራል። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የኖረባት ቦታ እንደሆነች ብዙ የሳይንሳዊ መረጃ ተግኝቷል። በበርሊን ጉባኤ በኩል የአውሮፓ ሀያላት ሀገሮች አፍሪካን ሲከፋፍሏት፣ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃለች። የሊግ ኦፍ ኔሽንስ League of Nations አባል ከነበሩት ሶስት የአፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነበረች። ከአጭር የኢጣልያ ወረራ ጊዜ በኋላም ከየተባበሩ ...

                                               

መንግሥተ ኢትዮጵያ

መንግሥተ ኢትዮጵያ ወይም አቢሲኒያ በዛሬዎቹ ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚገኝ መንግሥት ነበር። በትልቅነቱ ጊዜ ሰሜን ሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ደቡብ ግብፅ፣ ምሥራቃዊ ሱዳን፣ የመንና ምዕራባዊ ሳውዲ አረቢያን ያጠቃልል ነበር። ኢትዮቢያየኢትዮ ግዛትያ ግዛት የአረብ እና የቱርክ ጦርን ለማስመለስ እና ከብዙ የአውሮፓ አገራት ጋር ወዳጃዊ ግንኙነቶችን ለመጀመር በተከታታይ በቀጣይነት የሚተዳደር ነበር ፡፡ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ጋር ከተቀላቀለችበት 1936 እስከ 1941 ባለው ጊዜ ውስጥ አጭር ጊዜ ሳይጨምር በ 1882 በእንግሊዝ ግብፅ ወረራ የተጀመረውን የቅኝ ግዛት ለማስቀረት ብቸኛ የአፍሪካ ሀገሮች ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ ነበሩ ፡፡ ምስራቃዊ ጣሊያን። የቅኝ ግዛት ግዛቶች ከወደሙ በኋላ በሃያኛው ክፍለዘመን አጋማሽ ላይ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በንጉሠ ነገሥት ከሚተዳደሩ ሦስት የዓለም አገራት አንዷ እስከ 1974 ዓ.ም.

                                               

አርጎብኛ

አርጎብኛ ከደቡባዊ ሴሜቲክ ቋንቋወች አንዱ ነው። በአንድ ወገን በጥቂቱ ከ አማርኛ በሌላ ወገን ከ ሐረሪኛ ጋር ተመሳሳይ ቅርጽ ያለው ቋንቋ ነው። የአርጎባ ማህበረሰብ፣ በኢትዮጵያ በሰሜናዊ ክፍል ትግራይና ወሎ፣ በደቡብ እስከ ባሌ፣በምስራቅ እስከ ሐረር ቆላማ ስፍራና አፋር፣ ሰሜን ሸዋ አካባቢ የሚኖሩ ሕዝቦች ናቸው፡፡ አርጎባዎች በኤርትራም እንደሚኖሩ ሲጠቆም" ጀበርት” የሚል መጠሪያ አላቸው፡፡" አርጎቦ” የብሔረሰብ እና የቋንቋ መጠሪያ ነው፡፡ በ13ኛው ክፍለ ዘመን የይፋት ወላስማ ሥርወ መንግሥት ንግድን መሥርቶ በነበረ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን እስላማዊ መንግሥትን እንዳቋቋመ የሚገለጸው በኋላም በሁለተኛው ሂጅራ በነብዩ መሐመድ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከቁረሾች ጋር በነበረው ግጭት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ አረቦችን ተቀብሎ ያስተናገደ የመጀመሪያው የሙስሊም ማህበረሰብ የአርጎባ ማህበረሰብ እንደሆነም ይጠቁማሉ፡፡" አርጎብኛ” የሴሜቲክ ቋንቋ ዝርያ ሲሆን በውል የተለዩ ሁለት ዘዬዎች አሉት፡፡ የመጀመሪያው በደቡብ ወሎ አካባቢ የሚነገረው" ...

                                               

አቡጊዳ

ለፊልሙ፣ አቡጊዳ ፊልም ይዩ። አቡጊዳ ማለት ፊደል ነው። ከልሳነ ግዕዝ የተነሣ ነው። ቢሆንም በቅርብ ጊዜ አንዳንድ የፈረንጅ አገር ሊቅ ይህን አባባል ለቋንቋዎች ጥናት ተበድሯል። በዚሁ አነጋገር "አቡጊዳ" ማለት በዓለም የሚገኙ ልዩ አይነት ጽሕፈቶች ሊያመልከት ይችላል። በየአገሮቹ ፊደላቸው "አቡጊዳ" የሚባለው እያንዳንዱ ፊደል ለክፍለ-ቃል ለመወከል ሲሆን ነው እንጂ እንደ እንግሊዝኛ "አልፋቤት" ፊደሉ ለ1 ተነባቢ ወይም ለ1 አናባቢ ብቻ ሲሆን አይደለም። ስለዚህ የግዕዙ ፊደል ይሁንና ሌሎችም ለምሳሌ ብዙ የህንድ አገር አጻጻፎች ጨምረው አቡጊዳ በሚግድጅቭጅለው ስም ይታወቃሉ። ብራህሚክ ወይም ደቫናጋሪ በተባሉት የህንድ አጻጻፎች በኩል እያንዳንዱ ክፍለ-ቃል በተለየ ፊደል ሲወከል የአናባቢዎች መጠን የሚታየው የፊደሉን መልክ እንደ ግዕዝ ወይም እንደ አማርኛ ትንሽ በመቀየሩ ነው። ስለዚህ በቋንቋ ሊቃውንት ዘንድ አቡጊዳዎች ይባላሉ። በተጨማሪ፣ በካናዳ አገር ለጥንታዊ ኗሪ ቀይ ኢንዲያን የተባሉ ጐሣዎች ያላቸው አጻጻፍ እንደዚህ አይነት ነው፤ ...

                                               

ኢትዮጵስት በዓለም ዙሪያ

ኢትዮጵስት በዓለም ዙሪያ የኢትዮጵያ ጥናት ፡ ይህ ጥናት አጠቃላይ የሆነ የኢትዮጵያ የታሪክ ፣ የጆግራፊ፣ የዘር፣ የቋንቋ፣ የስነፅሁፍ፣ የባሕል፣ የተፈጥሮ ሐብት፣ የኤኮኖሚ፣ የፖለቲካና የሶሻል፣ ጥናቶችን ያጠቃልላል። ይህ ነጻ የሆነ ሳይንሳዊ ጥናት በቅርቡ ተጠናክሮ የቀጠለ ቢሆንም በቅድመ ጥናቶች የተደረጉ ስራወች እንደሚያሳዮት ጥናቶች የተከሃዱት ባጠቃላይ ፖቶሎጅካል የታሪክ፣ የቋንቋ፣ የባህልና በሀገሪቱ የሚኖሩ ጎሳወችን በተመለከተ ነበር። በመጀመሪያ የኢትዮጵስት ጥናተቶች የወጡት በ17ኛዉ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ሲሆን በ20ኛዉ ክፍለ ዘመን በአዉሮፓዉያን ቋንቋ በመጀመሪያ ጊዜ በኢጣሊያንኛ ከዚያም በፈረንሳይኛና በእንግሊዝኛ ስለትዮጵያ ጥናታዊ ጽሑፎች ብቅ ማለት ጀመሩ። ስለዚህም እንደምሳሌ የሚጠቀሰዉ ‘የኢትዮጵያ ጥናት‘ በሚል /studi etiopici; etudes ethiopiennes; Ethiopian studies/ በኢጣሊኛ ቋንቋ የሚታተም ጽሑፍ ነበር። የኢትዮጵስት የኢትዩጵያ ጥናት የሚለዉ ሀሳብ በተለይም ከመጀመሪያዉ ዓለም አቀፍ የኢ ...

                                               

ኩሽ (የካም ልጅ)

ኩሽ በ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 10 መሠረት ከኖህ ልጆች መካከል የካም በኩር ልጅ ነበረ። የኩሽ ልጆች ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማና ሰብቃታ ሲሆኑ ከዚህ በላይ የናምሩድ አባት ይባላል። የአይሁድ ታሪክ መምህር ፍላቭዩስ ዮሴፉስ 100 ዓ.ም. ገደማ እንደ ጻፉት፣ "ከካም አራት ልጆች፣ እድሜ የኩሽን ስም ከቶ አልጎዳምና፤ እርሱ የነገሠባቸው ኢትዮጵያውያን ዛሬውም ቢሆን በራሳቸውና በእስያም ሰዎች ሁሉ ዘንድ ኩሻውያን ይባላሉና።" ከጥንት ጀምሮ ታሪካዊው የኩሽ መንግሥት በአሁኑ ስሜን ሱዳን እንደ ኖረ ሊጠራጠር አይችልም። ይኸው ስያሜ ከቅድመኞቹ የግብጽ መዝገቦች ከ2 መንቱሆተፕ ዘመን ከ2092 ዓክልበ. ግድም ጀምሮ ታውቋል። በኋለኛ ዘመን "ኩሽ" ና የግሪክ ትርጉሙ Αιθιοπία /አይቲዮፒያ/ ከሳህራ ደቡብ ላለው ምድር በሰፊው ይጠቀም ነበር። ደግሞ በአፍሪቃ ቀንድ ዙሪያ የሚኖሩት ኩሺቲክ ሕዝቦች ሶማሌ፣ አፋር፣ ኦሮሞ፣አገው፣ቅማንት፣ስልጤ፣ጉራጌ፣ሲዳማ፣ጋሞና ሌሎች ይህን ስም ከዚሁ ኩሽ ተቀበሉ፤ ከተወላጆቹ መሃል ተቆጥረው ነው። አብዛኛው ጊዜ ...

ኢትዮጵያ ቅደሚ
                                               

ኢትዮጵያ ቅደሚ

ኢትዮጵያ ቅደሚ በኅብረተሰባዊነት አብቢ ለምልሚ! ቃል ኪዳን ገብተዋል ጀግኖች ልጆችሽ ወንዞች ተራሮችሽ ድንግል መሬትሽ ለኢትዮጵያ አንድነት ለነፃነትሽ መስዋዕት ሲሆኑ ለክብር ለዝናሽ! ተራመጂ ወደፊት በጥበብ ጎዳና ታጠቂ ለሥራ ላገር ብልጽግና! የጀግኖች እናት ነሽ በልጆችሽ ኩሪ ጠላቶችሽ ይጥፉ ለዘላለም ኑሪ! ግጥም: አሰፋ ገብረማርያም ዜማ: ዳንኤል ዮሐንስ

                                               

ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ መንግስት የበላይ ጠባቂነት የሚንቀሳቀስ የሀገሪቱ ብቸኛ የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው። ዜና፣ ስፖርት፣ ሙዚቃ፣ እና የመሳሰሉትን ስርጭቶች ለተመልካቾች ያቀርባል። ስርጭቱንም በአማርኛ፣ በትግርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በሶማልኛ፣ በአፋርኛ፣ በእንግሊዝኛ እና በአረብኛ ቋንቋዎች ያቀርባል። መቀመጫውን አዲስ አበባ ከተማ ያደረገ በአሁኑ ጊዜ ድርጅቱ በኢ.ቴ.ሬ.ድ. የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ድርጅት ስር የሚተዳደር ነው።

                                               

ጳጉሜ

ጳጉሜ የወር ስም ሆኖ በነሐሴ እና በመስከረም ወራት መኻል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ የመጨረሻው እና አሥራ ሦስተኛው የወር ስም ነው። "ጳጉሜ" በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዘመነ ዮሐንስ ሥግር ዓመት በመሆኑ ስድስት ዕለታት አሉት። በዘመነ ልቆስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና በዘመነ ማርቆስ አምስት ዕለታት አሉት። "ጳጉሜ" የሚለው ስም ምንጩ ከግሪክ ቋንቋ ሲሆን < > ማለት ነው። ነሐሴ የክረምት ሦስተኛው ወር ነው። ኢትዮጵያ በአለም ብቸኛዋ የ13 ወራት ጸጋ ባለቤት ናት። ይህ የፓጉሜን ወር በኢትዮጵያውያን ዘንድ የምህረት ወር ተብሎ ይታመናል። ወደ አዲስ አመት መግቢያ መሸጋገርያ ወርም ነው።

                                               

ጥር

ጥር የወር ስም ሆኖ በታኅሣሥ ወር እና በየካቲት ወር መሀከል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ አምስተኛው የወር ስም ነው። "ጥር" ከግዕዙ "ጠሐር / ጠሐረ" ከሚለው ቃል የተባዛ ነው። በቅብጢ አቆጣጠር የዚህ ወር ስም ቶቢ ነው። ይህም በጥንታዊ ግብጽ አረመኔ ሃይማኖት ከጣኦት ስም "ታዓበት" መሥዋዕት መጣ። በጎርጎርዮስ አቆጣጠር የጃንዩዌሪ መጨረሻና የፌብሩዌሪ መጀመርያ ነው።

                                               

ነሐሴ

ነሐሴ የወር ስም ሆኖ በሐምሌ እና በጳጉሜ ወራት መኻል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ አሥራ ሁለተኛው የወር ስም ነው። "ነሐሴ" ከግዕዙ "ነሐሰ" ከሚለው ቃል የመጣ ነው። ነሐሴ የክረምት ሦስተኛው ወር ነው።

                                               

አበሻ ስም

የአበሻ ስም በኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሚሰጥ ሲሆን አወቃቀሩ ከአረብ እና አይስላንድ አወቃቀር ጋር ተመሳሳይ ነው። አንድ ልጅ ሲወለድ ከሚወጣለት ስም በተጨማሪ በአባቱ እና በአባቱ ወንድ አያት ስም ይጠራል። በተለምዶ አሰያየሙ በአባት በኩል ቢሆንም በኤርትራ ውስጥ በእናት በኩል መሆን እንደሚችል የሚፈቅድ ሕግ ጸድቋል። የአበሻ ስም እንደ ምዕራባውያን የመጨረሻ ወይም የቤተሰብ ስም እንግሊዝኛ፦ last name / family name የለውም። በተጨማሪም ሴቶች ሲያገቡ ስማቸውን አይቀይሩም። በውጭ አገር የሚገኙ ዳያስፖራ አንዳንዴ የአባት ስማቸውን የመሃል ስም እንግሊዝኛ፦ middle name እና የአያት ስምን ደግሞ የቤተሰብ ስም አድርገው ይጠቀማሉ።

                                               

ኢንተርኔት በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ስርጭት አሁን ቢያንስ ለ15.4 % ሕዝብ ይደርሳል። ካለፉት አመታት ኢንተርኔት በኢትዮጵያ በጣም ተስፋፍቷል ማለት ነው። 2006 ዓም - 1.9 % 2007 ዓም - 3.7 % 2009 ዓም - 15.4 % 2000 ዓም - 0.4 %

                                               

የኢትዮጵያ መጓጓዣ

በኢትዮጵያ ጅማሮው ከማይታወቅበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ለረጅም አመታት የጋማ ከብቶች እንደ ዋና መጓጓዣነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። በአሁኑ ሰዓት በሰለጠኑት የሃገሪቱ ከተሞች የአየር ፣ የየብስ ብሎም የውሃ ላይ መጓጓዣዎች በጥቅም ላይ ውለው የሚታዩ ቢሆንም አሁንም በሃገሪቱ አብዛኛው ክፍል የጋማ ከብቶች በዋናነት ለመጓጓዣነት ብሎም ለጭነት አገልግሎትነት በመዋል ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ አርማ
                                               

የኢትዮጵያ ብሄራዊ አርማ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ አርማ ዛሬ ባለ 5 ጮራ ቢጫ ኮከብ ነው። ይህ አርማ የተቀየረው ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ በሃላ ነው። ከዚህ በፊት ለረጅም ጊዜ የነበረው ብሄራዊ አርማ ከላይ አረንጓዴ ከማህከል ደግሞ ቢጫ ከታች ደግሞ ቀይ ነበር። በመቀየሩም ብዙው የአገሪቱ ዜጎች ደስተኛ አይደሉም።

Free and no ads
no need to download or install

Pino - logical board game which is based on tactics and strategy. In general this is a remix of chess, checkers and corners. The game develops imagination, concentration, teaches how to solve tasks, plan their own actions and of course to think logically. It does not matter how much pieces you have, the main thing is how they are placement!

online intellectual game →