Топ-100
Back

ⓘ መሬት በሥርዓተ ፀሐይ ውስጥ ከፀሐይ ባላት ርቀት ሶስተኛ በግዝፈት ደግሞ ከፕላኔቶች ሁሉ አምስተኛ ግዙፍ የሆነች ፈለክ ናት። በግዝፈት እና በይዘት ቋጥኛዊ ይዘት ካላቸው ወይንም በእንግሊዝኛው ተሬስትሪያል ፈለኮች ከሚባሉት የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች። ..                                               

23/1978

                                               

ሐረግ መምዘዝ

                                               

ቅልልቦሽ

ቅልልቦሽ የኢትዮጵያ ህጻናት በጠጠር የሚጫወቱት ሲሆን አጨዋወቱም አንዱዋን ጠጠር ወደአየር በማጉናት እሱዋ ባየር ላይ እያለች የተቻለን ያክል ጠጠር ከመሬት ማፈስ ነው። ባየር ላይ ያለችው ጠጠር ስትመለስ በተጫዋቹ እጅ "መቀለብ" ወይም "መያዝ" ይኖርባታል። ሳትያዝ መሬት ላይ ከወደቀች፣ ጨዋታው አለቀ ማለት ነው። ጨዋታው "ጠጠር" በመባልም ይጠራል። ብዙ አይነት የቅልልብልቦሽ ጨዋታዎች ሲኖሩ፡ በጣም የታወቀው "ዓይጥ አለብሽ" በመባባል የሚጫወቱት ነው። ልጆቹ ሁለት ወይም ሶስት ይሆኑና፡ አምስት ቆንጆ ድብልብል ጠጠሮች፡ ስፋትና ርዝመታቸው ከግማሽ ኢንች የማይበልጡ፡ ይለቅሙና መሬት ይቀመጣሉ። ቀድሞ "ብጀ" ያለ መጀመርያ ይጀምራል። ብጀ ማለት ብጀምር ማለት ነው። ያንን ለማለት እሽቅድምድም ነው።"ብቀ" ያለ ከርሱ የሚከተል ነው ማለት ነው፡፡ ብቀ ማለት ብቀጥል ማለት ነው። ሁለት ልጆች እኩል "ብቀ" ካሉ በድምጽም ቢሆን ቀድሞ "ብ!" ከአፉ የወጣው ሰው ሁለተኛነቱን ያገኛል። "ብቀጣጥል!" ያለ ሶስተኛ ነው። "እንጀራ ብጋግር!" ያለ አራተ ...

                                               

የሐዋርያት ሥራ ፩

የሐዋርያት ሥራ ፩ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲሆን የሚያተኩረው በጌታችን በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርገትና እስከ ጰራቅሊጦስ መምጣት በፊት ሐዋርያት የሠሩት መንፈሳዊ ተግባራት ናቸው ። የጻፈውም ቅዱስ ሉቃስ እንደሆነ በማስረጃ ሙሉበሙሉ ቤተክርስቲያን የምታምነው ነው ይህም በ፳፮ ንዑስ ክፍሎች ይካተታል ።  የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፩

                                               

አሌ አላሌ

አሌ ሆይ አላሌ ሆይ ልጆች እግራቸውን ዘርግተው በመደዳ መሬት /ወለል ላይ ይቀመጣሉ። አጫዋች ወይም ከተጫዋቾቹ አንዱ የግር ጠቋሚ ይሆንና በሚዘመረው አንድ ቃል አንድ እግር ይጠቁማል። በመጨረሻው ቃል የሚጠቆመው እግር ይሰበሰብና ከጨዋታ ከጥቆማ ውጪ ይሆናል። ጨዋታው እየተደጋገመ ሁለቱም እግሩ የተጠቆመበት ቁልቢት ያረፈችበት ልጅ ከጨዋታው ይወጣል። እንዲህ እየተባለ አንድ ልጅ እስኪቀርና አሸናፊ እስኪሆን ጨዋታው ይቀጥላል። አሌ ሆይ አላሌ ሆይ ገረዴን አያችሁ ወይ ገረዴን ማርያም ስማ በርኩማ አሸክማ በርኩማ የዳገቴ የሸማ ቅዳዶቴ ቀድጄ ቀዳድጄ ሰጠኋት ላበልጄ አበልጅ ብትወደኝ ጨረቃ ሳመችኝ ጨረቃ ድንቡል ቦቃ አጤ ቤት ገባች አውቃ አጤ ቤት ያሉ ልጆች ፈተጉ ፈታተጉ በቁልቢት አስቀመጡ ቁልቢት ከስንዴ ቆሎ ከዳቦ ቆሎ ይችን ትተሽ ይቺን አንሺ ቶሎ አሌሆይ. አንድ እግር ይጠቆማል አላሌሆይ. ሁለተኛ እገር ይጠቆማል. ገረዴን.3ኛ እግር አያችሁ ወይ.4ኛ እግር.እንዲህ እያለ ይቀጥላል ይችን አንሺ ቶሎ ተብሎ የተጠቆመው እግር ይሰበሰባል፤ የተሰ ...

                                               

መሐረቤን ያያችሁ

መሓረቤን ያያችሁ ፦ ይህ፡ ልጆች መሮጥ ከቻሉበት ዕድሜ ጀምሮ፡ በቡድን ሆነው ሊጫወቱት የሚችሉት ጨዋታ ነው። ቁጥራቸው በርከት ብሎ፡ ትልቅ ክብ ሰርተው መቀመጥ ሲችሉ፡ ጨዋታውን መጫወት ይችላሉ። አጨዋወቱም፦ ልጆቹ ትልቅ ክብ ይሠሩና፡ እርስ በርስ እየተያዩ ይቀመጣሉ። አንድ መሓረብ የሚያክል፡ ሊወርወር የሚችል ጨርቅ ይዘጋጃል። ከዚያም፡ አንድ ልጅ ጨዋታውን ይጀምራል፤ ወይም፡ አብሮዋቸው ያለው ትልቅ ሰው ጨዋታውን ይጀምራል። መሓረቡን በእጁ ይዞ፡ ከጀርባቸው ክቡን እየተከተለ፡ ረጋ ብሎ፡ አንዱን እግሩን ሁለት ጊዜ መሬት እየጣለ፡ ሁለተኛውን እያስከተለ፡ "መሓረቤን ያያችሁ" እያለ ይሮጣል። ልጆቹ፡ "አላየንም ባካችሁ" እያሉ ቸብ እያደረጉ ይቀበሉታል። በዚህ መልክ አንድ ሁለቴ፡ ወይም እስኪዘናጉ ድረስ ይዞራቸዋል። "መሓረቤን ያያችሁ?" "አላየንም ባካችሁ!" "መሓረቤን ያያችሁ" "አላየንም ባካችሁ!" ከዘፈኑ እኩል ቸብ እየተደረገ ይዘፈናል። በመሓል፡ ሳያስታውቅበት፡ ከአንዱ ሕጻን ጀርባ፡ መሓረቡን ጣል ያደርግና፡ ምንም እንዳልተለወጠ በማስ ...

መሬት
                                     

ⓘ መሬት

መሬት በሥርዓተ ፀሐይ ውስጥ ከፀሐይ ባላት ርቀት ሶስተኛ በግዝፈት ደግሞ ከፕላኔቶች ሁሉ አምስተኛ ግዙፍ የሆነች ፈለክ ናት። በግዝፈት እና በይዘት ቋጥኛዊ ይዘት ካላቸው ወይንም በእንግሊዝኛው ተሬስትሪያል ፈለኮች ከሚባሉት የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች። በተለምዶ ዓለም ወይም ምድር እየተባለች ትጠራለች። በሳይንሳዊ የተለምዶ ስም ደግሞ "ሰማያዊዋ ፕላኔት" እየተባለች ትጠራለች። ይህች ፕላኔት የሰው ልጅን ጨምሮ ለብዙ ሚሊዮን ዝርያዎች መኖሪያ ናት። ከምድር ብዛት አትክልት ሁሉ እየበቀሉ ሲሆን ለሰው ልጅና ለእንስሳ ያስፈለጉት እህል፣ ፍራፍሬ፣ መድኃኒቶችና ሌሎችም ሁሉ ታስገኛለች። ይህም የታወቀች ብቸኛዋ ህይወት ያለው ነገር መኖሪያ ያደርጋታል። ስለዚህ ነው በተለያዩ እምነቶች ዘንድ ምድራዊት እማማችን የተባለች።

"አብርሃማዊ" በተባሉት ሃይማኖቶች በተለይ ክርስትና፣ እስልምናና አይሁድና ቅዱሳን መጻሕፍት እንደሚሉ፣ መጀመርያ ፪ ሰዎች አዳምና ሕይዋን ከኤደን ገነት ወጥተው የሰው ልጅ ታሪክ ከ6 ሺህ አመታት በላይ ብዙ አይሆንም። ከዚያ አስቀድሞ በገነት ያለፈው ዘመን ልክ ባይቆጠረም፣ ፍጥረቱ ከነምድርና ፀሐይ በ፯ "ጧቶች" ና "ምሽቶች" እንደ ተፈጸመ ስለሚባል፣ ባንድ ሳምንት ውስጥ እንደ ሆነ የሚያምኑ አሉ። ሆኖም ምድርና ፀሐይ በሥፍራቸው ሳይቀመጡ እነኚህ "ቀኖች" በእርግጥ የመሬት ፳፬ ሰዓት ቀኖች ነበሩ ማለት ያስቸግራል። ከተፈጠረች ያስቆጠረችው ዓመት በውል ባይታወቅም ግን በጊዜያችን ባሉት ሳይንሳዊ ዘዴዎች ባኩል የመሬት አማካይ እድሜ ወደ 4.6 ቢሊዮን ዓመታት ገደማ ይጠጋል። ከዚያን ጊዜ ወዲህ በ1 ቢሊዮን ዓመት ውስጥ ህይወት ያለው ነገር መኖሩ ይታሥባል።

                                     

1.1. የመሬት ውስጣዊ ክፍል ውጫዊ የመሬት ክፍል

የመጀመሪያው ውጫዊው የመሬት ክፍል ወይም በእንግሊዝኛው ክረስት የሚባለው ሲሆን የመሬት ቅርፊት ልንለው እንችላለን። በአብዛኛው ከተለያዩ የቋጥኝ አይነቶች የተገነባ ሲሆን ህይወት ያላቸው ነገሮች በሙሉ የሚኖሩት በዚህኛው የመሬት ክፍል ላይ ነው። ይህ ክፍል ውፍረቱን በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል። ምክንያቱ ደግሞ በውቅያኖሶች ስር ያለው የውፍረቱ መጠን እና በአህጉራት ላይ ያለው መጠን ስለሚለያይ ነው። የመሬት ቅርፊት በውቅያኖሶች ስር ያለው ውፍረት ከአምስት ሺህ ሜትር 3 ማይል እስከ አስር ሽህ ሜትር 6 ማይል ነው። ይህ ውፍረት በአህጉሮች ላይ ከሰላሳ ኪ.ሜ. 20 ማይል እስከ ሃምሳ ኪ.ሜ. 30 ማይል ነው።

                                     

1.2. የመሬት ውስጣዊ ክፍል መካከለኛው የመሬት ክፍል

ሁለተኛው የመሬት ክፍል መካከለኛው የመሬት ክፍል ወይም በእንግሊዝኛው ማንትል በመባል ይጠራል። ይህ የመሬት ክፍል ፈሳሻማ ይዘት አለው። ውፍረቱ እስከ 2890 ኪ.ሜ. 1800 ማይል ይደርሳል። የመሬትን 84 በመቶ 84% መጠን ይሆናል። በአብዛኛው በቅልጥ አለት ወይም ማግማ የተሞላ ነው። ይህም በእንቁላል የመካከለኛው ነጭ ፈሳሽ ይወከላል።

                                     

1.3. የመሬት ውስጣዊ ክፍል ውስጠኛው የመሬት ክፍል

የመጨረሻው እና ሶስተኛው ደግሞ ውስጠኛው የመሬት ክፍል ወይም በእንግሊዝኛው ኮር የሚባለው ነው። በእንቁላል የውስጠኛው አስኳል መወከል ይቻላል። እጅግ በጣም ሞቃት ሲሆን የፀሐይን የውጨኛ ክፍል መጠነ ሙቀት ይኖርዋል። ይህ ክፍል መጠኑ አነስተኛ ሲሆን በራዲየስ እስከ 1220 ኪ. ሜ. ብቻ ነው። በዚህም የጨረቃን መጠን 70 በመቶ 70% ጋር ይነጻጸራል።

                                     

2. የመሬት ታሪክ

የመሬትን ታሪክ ለማወቅ የተፈጥሮ ሳይንስ የበኩሉን ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህም የመሬት እድሜ ከ4.6 ቢሊዮን አመት ወዲህ ያሉትን አመታት በሙሉ የሚያጠቃልል ይሆናል። ይህም የጠቅላላ ሰማያዊ አካላት ወይም ዩኒቨርስ ን ሲሶ አንድ ሶስተኛ እድሜ ይሸፍናል። በዚህ ዘመን ነው እንግዲህ መልከዓ-ምድራዊም ሆነ ፍጥረታዊ ለውጦች የተከናወኑት። በአጠቃላይ የመሬትን ታሪክ ሳይንሳዊ በሆነ ወይም ሃይማኖታዊ በሆነ መልኩ ማየት ይቻላል። ሁለቱም በአሁኑ ጊዜ ተቀባይነት ያላቸው መላምቶች ናቸው። ደግሞ "ባለሙያ ንድፍ" ን ይዩ።

                                     

2.1. የመሬት ታሪክ ሃይማኖታዊ

የመጀመሪያው እና ከተመሰረተ ከሁለት ሺህ አመታት በላይ ያስቆጠሩት ሃይማኖታዊ እምነቶች አሉ። በነዚህ መሰረት መሬት የተፈጠረችው የአለም ፈጣሪና ጌታ በሆነው በእግዚአብሔር ወይም በአላህ ለሰው ልጆች መኖሪያ ተብሎ ነው የሚል እምነት አለው። ይህ እምነት በአብዛሃኛው የአለም ሃይማኖታዊ ህዝቦች ተቀባይነት ያለው ነው። ይዘቱም በተለያዩ የእምነት አይነቶች የተለያየ ፈጣሪ እንደመኖሩ የሚለያይ ነው። ለዚህ አስተሳሰብ ከሚወክሉት መሃል አንዱ የቅብጥ ተዋሕዶ ቄስ አባ ታድሮስ ማላቲ እንደሚሉት፣ በትምህርተ ሂሳብ ረገድ የመሬቲቱ ስፋት ለአንድ ሚልዮን አመታት የሰው ልጅ ትውልድ መበዛት በቂ ሊሆን ከቶ አይችልም። እያንዳንዱ ቤተሠብ በአማካኝ 3 ልጆች ብቻ ቢወልዱ በሚልዮን አመታት የመሬት ስፋት አንድ ሺህ እጥፍ ቢሆንም እንኳ አይበቃም ይላሉ። ስለዚህ የምድር እድሜ ስፍር ቁጥር የሌለው ረጅም ጊዜ ቢሆንም፣ የስው ልጅ ትውልድ ግን ከ6000 ሺህ አመታት በላይ ብዙ ሊሆን አይችልም ይላሉ።

                                     

3. ዘመናት

የመሬትን ታሪክ በመሬት ጥናት ወይም ጂኦሎጂ በተለያዩ ዘመናት ወይም በእንግሊዝኛው ኢራ ከፋፍሎ ማየት ይቻላል። ይህም ሁሉ የሚታሰበው ከሳይንሳዊ ሊቃውንት ሃልዮ ምርመራ ዘንድ ነው። እነዚህ ዘመናት በቢሊዮን እና ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አመታት እድሜ ያላቸው ሲሆኑ በተለያዩ አነስተኛ ዘመናት ወይም ፔሬድስ ይከፋፈላሉ። ጂኦሎጂ የመሬትን ታሪክ በአራት ዋና ዘመናት ወይም ኢራስ ከፍሎ ያያል። እነዚህም፦

  • አሁን ያለንበት ዘመን ወይም በእንግሊዝኛው Cenozoic Era ናቸው።
  • የመጀመሪያው ዘመን ወይም በእንግሊዝኛው Precambrian Era
  • ቅድመ ዘመን ወይም በእንግሊዝኛው Paleozoic Era
  • መካከለኛው ዘመን ወይም በእንግሊዝኛው Mesozoic Era እና
                                     

3.1. ዘመናት የመጀመሪያው ዘመን ወይም በእንግሊዝኛው Precambrian Era

ይህ ዘመን ከ4500 ሚሊዮን አመታት በፊት ያለው የመሬት እድሜ ነው። የመሬትን ሰባት ስምንተኛ እድሜ የሚያጠቃልል ነው። ነገር ግን ስለዚህ ዘመን ዘመናዊው ሳይንስ ማወቅ የቻለው ጥቂት ነገር ብቻ ነው። በዚህ ዘመን ህይወት ያለው ነገር ለመፈጠሩ የተገኙ መረጃዎች አነስተኛ ቢሆኑም በምዕራብ አውስትራሊያ 3.46 ቢሊዮን አመታት ያስቆጠረ ህዋስ ወይም ባክቴሪያ ተገኝቷል።

                                     

3.2. ዘመናት ቅድመ ዘመን ወይም በእንግሊዝኛው Paleozoic Era

ይህ ዘመን የሚሸፍነው ከ 542 ሚሊዮን እስከ 251 ሚሊዮን አመታት በፊት ያለውን የመሬት እድሜ ነው። የተለያዩ የዓሳ ዝርያዎችን ጨምሮ ትላልቅ የእንሽላሊት ዘሮች ወይም ዳይኖሰሮች በዘመኑ መገባደጃ አካባቢ ተከስተዋል።

                                     

3.3. ዘመናት አሁን ያለንበት ዘመን ወይም በእንግሊዝኛው Cenozoic Era

ከ65.5 ሚሊዮን አመታት በፊት ጀምሮ አሁን እስካለንበት ያለውን ጊዜ የሚሸፍነው ይህ ዘመን አብዛሃኛው የመሬት ለውጦች ተከናውነውበታል።

                                     

4. የመሬት ከባቢ አየር

የመሬት የከባቢ አየር በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ይዘቶች ነበሩት። በውስጡ የሚገኙት ህይወት ላላችው ነገሮች አስፈላጊ የሆኑ ነገርችም የኦዞን ንጣፍን ጨምሮ በየጊዜው ተለዋውዋል።ከባቢ አየራችን በውስጡ 78 በመቶ ናይትሮጅን፣ 21 በመቶ ኦክስጅን፣ 0.93 በመቶ አርገን፣ 0.038 በመቶ ካርቦን ክልቶኦክሳይድ የተባሉ ንጥረ ነገሮችን ጋዞችን በውስጡ ይዟል። አሁን ያለው ሁኔታ መሬት ለተጨማሪ 1.5 ቢሊዮን አመታት ህይወት ያላቸው ነገሮች እንዲኖሩባት ያስችላል ተብሎ ይታመናል።

                                     

5. የውጭ ማያያዣዎች

  • NASA Earth Observatory|በናሳ የመሬት ቅኝት
  • Climate changes cause Earths shape to change – NASA|የአየር ንብረት ለውጥ የመሬትን ቅርፅ ለውጦታል - ናሳ
  • USGS Geomagnetism Program|ዩ ኤስ ጂ ኤስ የጂኦማግኔቲዝም ፕሮግራም
  • Earth Profile በ NASAs Solar System Exploration
  • The Gateway to Astronaut Photography of Earth|የመሬት ልዩ ጠፈራዊ ምሥሎች
Free and no ads
no need to download or install

Pino - logical board game which is based on tactics and strategy. In general this is a remix of chess, checkers and corners. The game develops imagination, concentration, teaches how to solve tasks, plan their own actions and of course to think logically. It does not matter how much pieces you have, the main thing is how they are placement!

online intellectual game →